Content-Length: 65205 | pFad | https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%88%89%E1%8B%8B%E1%88%9D%E1%8A%93

ውክፔዲያ - አሉዋምና Jump to content

አሉዋምና

ከውክፔዲያ
የአሉዋምና ማኅተም

አሉዋምና ምናልባት ከ1483 እስከ 1478 ዓክልበ ድረስ ዓክልበ. አካባቢ ከታሑርዋይሊ በኋላ በሐቱሳሽ (በሐቲ አገር ወይም የኬጥያውያን መንግሥት) የገዛ ንጉሥ እንደ ነበር ይታስባል። (ሆኖም ታሑርዋይሊ ከአሉዋምና ወይም ከ2 ሐንቲሊ ቀጥሎ እንደ ነገሠ የሚል አስተሳሰብ ደግሞ ብዙ ይታያል።)

ተለፒኑ በጻፈው የተለፒኑ ዐዋጅ በተባለው ሰነድ ዘንድ፣ ወንድ ልዑል አልጋ ወራሽ ባይኖር ኖሮ የትልቅዋ ሴት ልጅ ባለቤት ዘውዱን ወርሶ እሱ ንጉሥ ይሁን የሚል ነው። እንዲያውም የተለፒኑ ወንድ ልጅ ልዑል አሙና አርፎ ስለዚህ የሴት ልጁ የሐራፕሺሊ (ወይም ሐረፕሼኪ) ባል አሉዋምና የተለፒኑ ሕጋዊ ወራሽ ይሆን ነበር። ሆኖም ከዚህ አዋጅ በኋላ አሉዋምናና ሐረፕሼኪ በአባትዋ በተለፒኑ መንግሥት ላይ አምጸው ወደ ማሊታሽኩር እንደ ተሳደዱ ይመስላል። ስለዚህ የታሑርዋይሊ ዘመን የቀደመው ይሆናል። ብዙ ጊዜ ሳያልፍ ግን አሉዋምናና ንግሥቱ ሐረፕሼኪ ዙፋናቸውን እንዳገኙ ይመስላል።

ኬጥኛ ኩኔይፎርም «አሉዋምና ታላቅ ንጉሥ፣ ታባርና» የሚሉ ማኅተሞቹ ለሥነ ቅርስ ታውቀዋል። ስንት አመት እንደ ነገሠ በእርግጡ አይታወቅም። እንዲሁም ንጉሥ አሉዋምና ለወራሹ ልጅ ለ2 ሐንቲሊ የመሬት ርስት የሚሰጥበት ሰነድ ተገኝቷል።

ቀዳሚው
ታሑርዋይሊ
ሐቲ ንጉሥ
1483-1478 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
2 ሐንቲሊ








ApplySandwichStrip

pFad - (p)hone/(F)rame/(a)nonymizer/(d)eclutterfier!      Saves Data!


--- a PPN by Garber Painting Akron. With Image Size Reduction included!

Fetched URL: https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%88%89%E1%8B%8B%E1%88%9D%E1%8A%93

Alternative Proxies:

Alternative Proxy

pFad Proxy

pFad v3 Proxy

pFad v4 Proxy