Content-Length: 90877 | pFad | https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%AA%E1%88%BD

ውክፔዲያ - ኪሽ Jump to content

ኪሽ

ከውክፔዲያ
ኪሽ ከተማ በስሜን ሱመር

ኪሽሱመር (የዛሬው ኢራቅ) ጥንታዊ ከተማ ነበረ።

የሱመር ነገሥታት ዝርዝር በተባላው ሰነድ ዘንድ፣ ከማየ አይኅ በኋላ መጀመርያው ነገሥታት የነበሩበት ከተማ ኪሽ ሲሆን መጀመርያው ንጉሣቸው ጙሹር ነበር። የጙሹርም ተከታይ ኩላሢና-ቤል ሲባል፣ ይህ ስያሜ ግን በአካድኛ «ሁላቸው ባል (ሆኑ)» የሚለው ዓረፍተ ነገር ነው። ምናልባት በኪሽ መሃል ሥልጣን አለመኖሩን ለማመልከት እንደ ጠቀመ ይታስባል። በሰነዱ የሚከተሉት 9 ስሞች ደግሞ ሁላቸው በአካድኛ የእንስሳት ስሞች ናቸው (ለምሳሌ ዙቃቂፕ («ጊንጥ»)። አካድኛ ሴማዊ ቋንቋ እንደ መሆኑ መጠን፣ ይህ ከጥንት ጀምሮ የኪሽ ኗሪዎች በሰፊው ሴማውያን እንደ ጠቀለሉ ያሳያል።[1] ሆኖም ለነኚህ ቅድመኞች ነገሥታት አንዳችም ሌላ ቅርስ ስላተገኘላቸው፣ ታሪካዊ መሆናቸው አጠያያቂ ነው።

በዝርዝሩ ላይ 12ኛው የኪሽ ንጉሥ፣ ኤታና፣ «ወደ ሰማይ ዐርጐ ውጭ አገሮችን ሁሉ ያሠለጠነው» ይባላል። ለርሱም ኅልውና የቅርስ ማረጋገጫ ገና ባይገኝም፣ ስሙ ከአንዳንድ ሌላ የትውፊት ጽላት ይታወቃል። አንዳንዴም ይህ ኤታና የኪሽ መጀመርያው ንጉሥና መስራች ይባል ነበር።

በዝርዝሩ 21ኛው ንጉሥ፣ ኤንመባራገሲ፣ «የኤላምን ጦር ያጠፋው» ይባላል። የርሱ መንግሥት መጀመርያው በሥነ ቅርስ የተረጋገጠ ነው። ኤንመባራገሲ እንደገና በሌላ ትውፊት ይታወቃል፤ እርሱና ልጁ አጋ የኪሽ ንጉሶች በሆኑበት ወቅት፣ የኡሩክ ነገሥታት ዱሙዚድ አሣ አጥማጁ እና ጊልጋመሽ ተወዳዳሪዎቻቸው እንደ ነበሩ ይባላል።

በዚህ ድሮ ዘመን አንዳንድ የኪሽ ንጉሥ ከሥነ ቅርስ ቢታወቅም በሱመር ነገሥታት ዝርዝር ግን አይገኙም። ከነዚህም መካከል የኪሽ ንጉሥ ኡቱግ ወይም ኡሁብ ሐማዚን እንዳሸነፈ የሚል ቅርስ አለ፤ ደግሞ የኪሽ ንጉሥ መሲሊም መቀደሶችን በአዳብና በላጋሽ ከተሞች እንዳሠራ የሚሉ ቅርሶች አሉ።

በኋላ የኪሽ ሥልጣን ደክሞ፣ ከተማው ለሌሎች የከተማ-አገር መንግሥታት ይወድቅ ነበርና አይነተኛ ከተማ እንደ መሆኑ፣ «የኪሽ ንጉሥ» የሚለውም አርእስት እንደ ትልቅ ማዕረግ ተቆጥሮ፣ እነዚህ የሌሎች ከተሞች ነገሥታት ለራሳቸው ወገን «የኪሽ ንጉሥ» ይባሉ ጀመር። ለምሳሌ የኡር ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳ «የኪሽ ንጉሥ» ደግሞ ይባል ነበር። ታዋቂው የአካድ መንግሥት ንጉስ ታላቁ ሳርጐን ከኪሽ ዙሪያ ነበር።

በዚህ ጥንታዊ ዛጎል የተቀረጸው ጽሕፈት በአካድኛ «ሪሙሽ የኪሽ ንጉሥ» ይላል።

የውጭ መያያዣዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  1. ^ Cambridge Ancient History, p. 100








ApplySandwichStrip

pFad - (p)hone/(F)rame/(a)nonymizer/(d)eclutterfier!      Saves Data!


--- a PPN by Garber Painting Akron. With Image Size Reduction included!

Fetched URL: https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%AA%E1%88%BD

Alternative Proxies:

Alternative Proxy

pFad Proxy

pFad v3 Proxy

pFad v4 Proxy