Content-Length: 121933 | pFad | https://am.wikipedia.org/wiki/H

ውክፔዲያ - H Jump to content

H

ከውክፔዲያ
የላቲን አልፋቤት
A B C D E F
G H I J K L M
N O P Q R S T
U V W X Y Z
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

H / hላቲን አልፋቤት ስምንተኛው ፊደል ነው። በእንግሊዝኛ የፊደሉ ስም አጠራር /ኧይች/ ቢሆንም፣ የተናባቢው ድምጽ /ህ/ ያሰማል።

ግብፅኛ
ሰፐአት
ቅድመ ሴማዊ
ሔት
የፊንቄ ጽሕፈት
ሔት
የግሪክ ጽሕፈት
ሄታ/ኤታ
ኤትሩስካዊ
H
ላቲን
H
N24

የ«H» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ሔት» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የአጥር ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ።

በፊንቄ ጽሕፈት የፊደሉ ሔት ድምጽ እንደ ተናባቢ («ሕ») ሲሆን በግሪክ አልፋቤት እንዲሁም ሄታ ለ «ህ» ተጠቀመ። ከ450 ዓክልበ. ግድም በኋላ ግን ይህ ምልክት ትንሽ ተቀይሮ «ኤታ» (Η η) የአናባቢ ድምጽ «ኤ» ለማመልከት ይጠቅም ጀመር። ይህን ለውጥ መጀመርያ ያደረገው ባለቅኔው ሲሞኒዴስ ዘኬዮስ (564-476 ዓክልበ.) እንደ ነበር በግሪክ ጽሐፊዎች ተባለ። ሆኖም በጥንታዊ ጣልያን አልፋቤቶች እንደ ኤትሩስካዊ አልፋቤት እና ላቲን አልፋቤት፣ «H» ተናባቢውን «ህ» በመወክል ቆየ።

ግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ሐ» («ሐውት») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ሔት» ስለ መጣ፣ የላቲን «H» ዘመድ ሊባል ይችላል።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ H የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።








ApplySandwichStrip

pFad - (p)hone/(F)rame/(a)nonymizer/(d)eclutterfier!      Saves Data!


--- a PPN by Garber Painting Akron. With Image Size Reduction included!

Fetched URL: https://am.wikipedia.org/wiki/H

Alternative Proxies:

Alternative Proxy

pFad Proxy

pFad v3 Proxy

pFad v4 Proxy